የሕይወት ዓላማ ምንድር ነው?

ይህ ጥያቄ ለዘመናት ሲጠየቅ ኖሮአል።
መጽሐፍ ቅዱስ ግልጽ መልስ ይሰጠናል

የሕይወት ዋና ጉዳይ
ግንኙነት ነው።

ከዘፍጥረት እስከ ዮሐንስ ራእይ ድረስ መጽሐፍ ቅዱስ የሚያካፍለው የግንኙነት መልእክትን ነው። ይህ መልእክት ወንጌል (መልካም ዜና) ይባላል።
አንድ ሰው ይህን መልእክት ሲገነዘብና የእግዚአብሔርን የዘላለም ሕይወት ስጦታ ሲቀበል፥ የሕይወትን ዓላማ ብቻ ሳይሆን ሕይወትን ራሱን ያገኛል።

‘ኢየሱስም፦ እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤’ አለ፤ (ዮሐ. 14፥6)።

የዘላለም ሕይወትን መቀበል እንዴት እችላለሁ?

አንድ ሰው የዘላለም ሕይወትን የሚቀበለው ኢየሱስ ባደረገለት ነገር ላይ እምነቱን ሲያደርግ ነው። ኢየሱስ ላንተ ምን አደረገልህ? እርሱ በመስቀል ላይ ስለ ኃጢአትህ ሞተልህ፤ የዘላለም ሕይወት ይኖርህ ዘንድ ደግሞ ከሙታን ተነሣ፤ ደግሞም ኃጢአታቸውን ተናዝዘው በክርስቶስ እምነታቸውን ለሚያደርጉ ሁሉ የዘላለም ሕይወትን ይሰጣቸዋል።
‘በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤’ ዮሐ. 3፥36

የእርቅ ግንኙነት ቀላል በሆነ ጸሎት ሊጀምር ይችላል።

ኢየሱስን መከተል የማያልቅ ጉዞ ነው፤ ሆኖም በቀላል ጸሎት መጀመር ይችላል። ይህንን ጸሎት እንደ መጀመሪያ መሪ ጸሎት አድርገህ ተጠቀመው።

“God, I know that I’ve sinned. I recognize that my sin has separated me from you. I believe that Jesus died on the cross for my sin and that He rose again on the third day. As best I know how I turn from my sin by placing faith in what Jesus has done for me. In Jesus’ name, I pray, Amen.”
ዛሬ እምነትህን በኢየሱስ ላይ አድርገህ ከሆነ፥ ይህንን እምነትህን ለሌሎች እንድታካፍ እናበረታታሃለን።

እሺ አምናለሁ፤
ቀጥሎስ?

ይህንን ግንኙነትህን ከእግዚአብሔር ጋር ስትጀምር ይህን ጉዞ እንድትቀጥል የሚረዱህን ነገሮች ልናካፍልህ እንወድዳለን። ስለ ደኅንነት ጥያቄዎች ቢኖሩህ ወይም ይህንን፥ ‘ወንጌሉ ይህ ነው’ የተባለውን ትምህርት ለሌላ ሰው ወይም ቡድን ልታካፍል ብትወድድ፥ ‘ጥሪው’ ከሚለው ጀምር። ኢየሱስን መከተልን እየተማርክ ከሆነ፥ ‘ግንኙነት’ ከሚለው ጀምርና፥ ‘መከተል’ በሚለው ቀጥል፤ ከዚያም፥ ‘ጉዞው’ በሚለው ጨርስ።

See the Impact

Since 2012, we have been on a mission to see gospel transformation globally. These numbers represent the data collected through trainings and received from organizations using This Is The Gospel.
Translations of This is the Gospel are accessible to 4.9 billion people or 61% of the world’s population.
0
Pastors & Ministry Leaders Trained Globally
0
Professions of Faith
0
People Baptized
0
New Churches Planted
0
Translations of This is the Gospel are accessible to 4.9 billion people or 61% of the world’s population.
0
Pastors & Ministry Leaders Trained Globally
0
Professions of Faith
0
People Baptized
0
New Churches Planted
0